#ደጃዝማች_አያሌው ~~~~~~~~~~~~~~~~ [ዳንኤል ክብረት] ------------- በ20ኛው መ.ክ.ዘ ከተነሡት ኃያላን መኳንንት አንዱ ናቸው፡፡ የ #የራስ_ብሩ_ወልደ_ገብርኤል ልጅና የ #እቴጌ_ጣይቱ ዘመድ ሲሆኑ የወገራ አውራጃ ሹም፣ የስሜን አውራጃ ገዥ፣ #ልጅ_ኢያሱ ከተያዙ በኋላ ደግሞ የንጉሠ ነገሥቱ ጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡ #ደጃዝማች_አያሌው ብሩ #ንጉሥ_ኃይለ_ሥላሴ ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ሰዎች መካከል ናቸው፡፡ #መኢሶ ላይ ከ #ልጅ_ኢያሱ ጦር ጋር በተደረገው ጦርነት #ተፈሪ_መኮንን እንዲያሸንፉ #ደጃዝማች_አያሌው ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው፡፡ #ራስ_ጉግሣን ለመያዝ አንቺም ላይ በተደረገው ውጊያም የ #ደጃዝማች_አያሌው ጀግንነት ወሳኝ ነበር፡፡ እንዲያውም በዚህ ጦርነት ለሚያበረክቱት ውለታ የራስነትን ማዕረግ እንደሚያገኙ ከ #ንጉሥ_ተፈሪ ቃ